ለመሣሪያው ሥራ ላይ የሚውለው የሰዓት ሰቅ ይገልጻል። ተጠቃሚዎች ለአሁኑ ክፍለ-ጊዜ የተገለጸውን ሰዓት ሰቅ መሻር ይችላሉ። ይሁንና፣ ተዘግቶ ሲወጣ ወደተገለጸው የሰዓት ሰቅ ይቀለበሳል። ልክ ያልሆነ እሴት ከተሰጠ መመሪያው አሁንም በምትኩ «ጂኤምቲ» በመጠቀም ገቢር ይሆናል። ባዶ ሕብረቁምፊ ከተሰጠ መመሪያው ችላ ይባላል።
ይህ መመሪያ ሥራ ላይ ካልዋለ የአሁኑ ገቢር የሰዓት ሰቅ በሥራ ላይ እንዳለ ይቆያል፣ ይሁንና ተጠቃሚዎች የሰዓት ሰቁን ቀይረው ለውጡንም ቋሚ ማድረግ ይችላሉ። ስለዚህ፣ በአንድ ተጠቃሚ የተደረገ ለውጥ በመግቢያ ገጹ እና በሌሎች ተጠቃሚዎች ሁሉ ላይ ተጽዕኖ አለው።
አዲስ መሣሪያዎች የሰዓት ሰቃቸው ወደ «አሜሪካ/ፓሲፊክ» ተዋቅሮ ይጀምራሉ።
የእሴቱ ቅርጸት በ«IANA Time Zone Database» («https://en.wikipedia.org/wiki/Tz_database» ይመልከቱ) ውስጥ ያሉ የሰዓት ሰቆች ስሞችን ነው የሚከተለው። በተለይ ደግሞ አብዛኛዎቹ የሰዓት ሰቆች በ«አህጉር/ትልቅ_ከተማ» ወይም «ውቅያኖስ/ትልቅ_ከተማ» ሊጠቀሱ ይችላሉ።
ይህን መመሪያ ማዋቀር የሰዓት ሰቅን በራስ-ሰር በመሣሪያ አካባቢ ማግኘትን ያሰናክላል። እንዲሁም የSystemTimezoneAutomaticDetection መመሪያውንም ይሽረዋል።
Registry Hive | HKEY_LOCAL_MACHINE |
Registry Path | Software\Policies\Google\ChromeOS |
Value Name | SystemTimezone |
Value Type | REG_SZ |
Default Value |