የባለከፍተኛ ንፅፅር ሁነታ ተደራሽነት ባህሪው ነባሪ ሁኔታ በመግቢያ ገጹ ላይ ያዋቅሩት።
ይህ መመሪያ ወደ እውነት ከተዋቀረ የመግቢያ ገጹ ሲታይ ባለከፍተኛ ንፅፅር ሁነታው ይነቃል።
ይህ መመሪያ ወደ ሐሰት ከተዋቀረ የመግቢያ ገጹ ሲታይ ባለከፍተኛ ንፅፅር ሁነታው ይሰናከላል።
ይህ መመሪያ ከአዋቀሩት ተጠቃሚዎች ባለከፍተኛ ንፅፅር ሁነታን በማንቃት ወይም በማሰናከል ለጊዜው ሊሽሩት ይችላሉ። ይሁንና፣ የተጠቃሚው ምርጫ ዘላቂ አይደለም፣ እና የመግቢያ ገጹ እንደ አዲስ በታየ ቁጥር ወይም ተጠቃሚው በመግቢያ ገጹ ላይ ለአንድ ደቂቃ ስራ ከፈታ ነባሪው ወደነበረበት ይመለሳል።
ይህ መመሪያ እንዳልተዋቀረ ከተተወ የመግቢያ ገጹ መጀመሪያ ላይ ሲታይ ባለከፍተኛ ንፅፅር ሁነታው ይሰናከላል። ተጠቃሚዎች በማንኛውም ጊዜ ባለከፍተኛ ንፅፅር ሁነታውን ማንቃት ወይም ማሰናከል ይችላሉ፣ እና በመግቢያ ገጹ ላይ ያለው ሁኔታው በተጠቃሚዎች መካከል ቋሚ ይሆናል።
Registry Hive | HKEY_LOCAL_MACHINE |
Registry Path | Software\Policies\Google\ChromeOS |
Value Name | DeviceLoginScreenDefaultHighContrastEnabled |
Value Type | REG_DWORD |
Enabled Value | 1 |
Disabled Value | 0 |