በተለዋጭ አሳሹ የሚከፈቱ አስተናጋጆች

በተለዋጩ አሳሽ የሚከፈቱ የአስተናጋጅ ጎራ ስሞች ዝርዝር እንዲጠቅሱ ያስችልዎታል።

መመሪያው ከነቃ ወደ ተለዋጭ አሳሹ የሚደረገውን ሽግግር የሚያስጀምሩ የማጣሪያዎች ዝርዝር ማቅረብ ይኖርብዎታል። እያንዳንዱ ግቤት ከሚከተሉት አራት ዓይነቶች አንዱን መሆን ይኖርበታል፦

የአስተናጋጅ ስም ክፍል፦ እንደ «www.example.com» ያሉ የተሟሉ የጎራ ስሞች፣ ወይም እንደ «example.com» ያሉ የእነርሱ ክፍሎች፣ ወይም እንዲያውም «example» መጠቀስ አለባቸው። ልቅ ምልክቶች እስካሁን የተደገፉ አይደሉም።
የዩአርኤል ቅድመ-ቅጥያ፦ ካስፈለገ ትክክለኛ የዩአርኤል ቅድመ-ቅጥያዎች ብቻ ናቸው ከፕሮቶኮሉ እና ከወደቡ ጋር የሚዛመዱት። ምሳሌ፦ «http://login.example.com» ወይም «https://www.example.com:8080/login/»።
አሉታዊ ግቤት፦ በ«!» ይጀምር እና ከላይ እንደተገለጸው እንደ አስተናጋጅ ስም ክፍል ወይም የዩአርኤል ቅድመ-ቅጥያ ይቀጥላል። አሉታዊ ግቤቶች ሁልጊዜ በChrome ውስጥ ነው የሚከፈቱት። ምሳሌ፦ «!example.com » ወይም «!file:///c:/localapp/»።
የልቅ ምልክት ግቤት፦ አንዲት ነጠላ የ«*» ቁምፊ ብቻ ይይዛል። ከማንኛውም ዩአርኤል ጋር ይዛመዳል። አብዛኛዎቹ ዩአርኤሎች በተለዋጩ አሳሽ መከፈት እና ትንሽ የተመረጡ ዩአርኤሎች ብቻ በChrome ውስጥ መከፈት ካለባቸው ከአሉታዊ ግቤቶች ጋር አንድ ላይ ጥቅም ላይ እንዲውል የታሰበ ነው።

ጥቂት ክፍሎች በChrome ውስጥ እንዲከፈቱ በማስቀመጥ የአንድን ጎራ አብዛኛዎቹን ክፍሎች በተፈቀደላቸው ዝርዝር ላይ ማስቀመጥ ከሚያስችሉት ከአዎንታዊ ግቤቶች ይልቅ አሉታዊ ግቤቶች ከፍተኛ ተቀዳሚነት ደረጃ አላቸው።
የልቅ ምልክት ግቤት ካለ ሌሎች ደንቦች ከተረጋገጡ በኋላ ብቻ ነው ተፈጻሚ የሚሆነው።

የሚከተሉት ፕሮቶኮሎች አቅጣጫን ለማስቀየር ቁጥጥር ይደረግባቸዋል፦ http:፣ https:።

ሳይጠቀስ ከቀረ ወይም ባዶ ከተተወ - ወደ ተለዋጭ አሳሹ ምንም ዓይነት ሽግግር እንዲጀምር አይደረግም።

Supported on: Microsoft Windows XP SP2 ወይም ከዚያ በኋላ

በተለዋጭ አሳሹ የሚከፈቱ አስተናጋጆች

Registry HiveHKEY_LOCAL_MACHINE
Registry PathSoftware\Policies\Google\Chrome\3rdparty\Extensions\heildphpnddilhkemkielfhnkaagiabh\policy\url_list
Value Name{number}
Value TypeREG_SZ
Default Value

legacybrowsersupport.admx

Administrative Templates (Computers)

Administrative Templates (Users)