ተጠቃሚው በGoogle Chrome ውስጥ ሊያነቃቸው ወይም ሊያሰናክላቸው የሚችላቸው የተሰኪዎች ዝርዝር ይገልጻል።
የልቅ ምልክት ቁምፊዎች «*» እና «?» የዘፈቀደ ቁምፊዎች ተከታታዮችን ለማዛመድ ስራ ላይ መዋል ይችላሉ። «*» አንድ የዘፈቀደ የሆነ የቁምፊዎች ብዛት የሚያዛምድ ሲሆን «?» ደግሞ አማራጭ የሆነ ነጠላ ቁምፊን ያዛምዳል፣ ማለትም ዜሮ ወይም አንድ ቁምፊዎችን ያዛምዳል። የማምለጫ ቁምፊው «\» ነው፣ ስለዚህ ትክክለኛዎቹ የ«*» «?» ወይም «\» ቁምፊዎችን ለማዛመድ «\»ን ከፊታቸው ማስገባት አለብዎት።
ይህን ቅንብር ካነቁት የተገለጸው የተሰኪዎች ዝርዝር በGoogle Chrome ውስጥ ስራ ላይ መዋል ይችላሉ። ተጠቃሚዎች እነሱን በ«about:plugins» ውስጥ ማንቃት ወይም ማሰናከል ይችላሉ፣ ተሰኪው በDisabledPlugins ውስጥ ካለው ስርዓተ-ጥለት ጋር የሚዛመድ ቢሆንም። ተጠቃሚዎች እንዲሁም በDisabledPlugins፣ DisabledPluginsExceptions እና EnabledPlugins ውስጥ ካሉ ማንኛቸውም ስርዓተ-ጥለቶች ጋር የማይዛመዱ ተሰኪዎችንም ማሰናከል እና ማንቃት ይችላሉ።
ይህ መመሪያ «DisabledPlugins» እንደ ሁሉንም ተሰኪዎች «*» አሰናክል ወይም ሁሉም የJava ተሰኪዎች «*Java*» አሰናክል ያሉ በልቅ ምልክት የተቀመጡ ግቤቶችን ሲይዝ ነገር ግን አስተዳዳሪው እንደ «IcedTea Java 2.3» ያሉ የተወሰኑ ስሪቶችን ለማንቃት በሚፈልግበት ጊዜ በጥብቅ የተሰኪ ክልክል ዝርዝርን ለማስቻል የታሰበ ነው። እነኚህ የተወሰኑ ስሪቶች በዚህ መመሪያ ውስጥ ሊገለጹ ይችላሉ።
ሁለቱም የተሰኪው ስም እና የተሰኪው የቡድን ስም መካተት እንደሌለባቸው ልብ ይበሉ። እያንዳንዱ የተሰኪ ቡድን በabout:plugins ውስጥ በተለየ ክፍል ውስጥ ይታያል፤ እያንዳንዱ ክፍል አንድ ወይም ተጨማሪ ተሰኪዎች ሊኖረው ይችላል። ለምሳሌ፣ የ«Shockwave Flash» ተሰኪ በ«Adobe Flash Player» ቡድን ውስጥ ሲሆን፣ ያ ተሰኪ በክልክል ዝርዝር ውስጥ ላለመካተት የሁለቱም ስሞች ባልተካተቱት ላይ ተዛማጅ ሊኖራቸው ይገባል።
ይህ መመሪያ እንዳልተዋቀረ ከተተወ በ«DisabledPlugins» ውስጥ ካሉ ስርዓተ-ጥለቶች ጋር የሚዛመድ ማንኛውም ተሰኪ እንደተሰናከለ ይቆለፍና ተጠቃሚው ሊያነቃቸው አይችልም።
Registry Hive | HKEY_LOCAL_MACHINE or HKEY_CURRENT_USER |
Registry Path | Software\Policies\Google\Chrome\DisabledPluginsExceptions |
Value Name | {number} |
Value Type | REG_SZ |
Default Value |